ማርገዝ ለሚፈልጉ ጠቃሚ የእርግዝና መረጃ፡ (ዝም ብሎ ግንኙነት ስላደረጉ ብቻ እርግዝና አይመጣም!)

Semonun ሰሞኑን
Semonun ሰሞኑን
85.7 هزار بار بازدید - 5 سال پیش - እርግዝና እንዴትና መቼ? ጠቃሚ መረጃዎችን
እርግዝና እንዴትና መቼ? ጠቃሚ መረጃዎችን አቀናጅተን አቅርበንላችኋል!

ከእርግዝና ፣ ልጅ አስተዳደግ እና ቤተሰብ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ በርካታ ቪዲዮዎችን በየጊዜው ፖስት ስለምናደርግ ሰብስክራይብ በማድረግ ደምበኛ ይሁኑ! በተጨማሪም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸዉን ሌሎችም ለህይወታችን መልካም የሆኑ ጽሁፎች www.semonun.com እና www.facebook.com/semonun ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። በቪዲዮዎቻችን እንድንዳስሳቸዉ የምትፈልጉት ርእስ ካለ በአስተያየት አካፍሉን።
#እርግዝና #እርግዝናመረጃ #semonun
SEMONUN: Home of Pregnancy Related Information in Amharic
ስለ እርግዝና መረጃ፣ ስለርግዝና መረጃ፣ ስለእርግዝና መረጃ፤ እርግዝና በስንት ቀን ይታወቃል
እርግዝና እንዴትና መቼ?

እርግዝና እንዴትና መቼ እንደሚከሰት ማወቅ ማርገዝ ለሚፈልጉም ሆነ ለማይፈልጉ ጠቀሜታው የላቀ ነው፡፡ ማርገዝ ለሚፈልጉ ጊዜና ሁኔታዎችን አመቻችቶ ለመሞከር ሲረዳ ለማይፈልጉ ደግሞ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ለመጠንቀቅ ያግዛቸዋል፡፡ ይሁንና ካልተፈለገ እርግዝና ለመጠበቅ ወይም አራርቆ መዉለድ ለሚሹ የእርግዝና መከላከያ መውሰድ ዋነኛው መፍትሄ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

በአንድ የወር አበባ ኡደት ውስጥ ለፈርቲላይዜሽን(ለእርግዝና) የደረሰ የሴት እንቁላል ከመቀመጫው ከኦቫሪ ወጥቶ በማህጸን ቱቦ አድርጎ ወደ ማህጸን ይጓዛል፡፡ ይህ ሂደት ኦቩሌሽን ይባላል፡፡ በመደበኛነት አንድ ሴት ኦቩሌት የምታደርገው በአንድ የወር አበባ ኡደት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከኦቫሪ የወጣው እንቁላል ለፈርቲላይዜሽን(ለእርግዝና) ብቁ ሆኖ በማህጸን ቱቦ ውስጥ የሚቆየው ከ12 እስከ 24 ሰአት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከወንድ ዘር ጋር ተገናኝቶ እርግዝና ካልተፈጠረ እንቁላሉ ከማህጸን ግድግዳ ጋር አብሮ በወር አበባ መልክ ይወገዳል፡፡

ኦቩሌት የሚደረግበትን ጊዜ ማወቅ ቶሎ ለማርገዝ ይረዳል፡፡ አንዲት ሴት ኦቩሌት የምታደርግበትን ጊዜ በእርግጠኛነት መናገር ባይቻልም ለመገመት የሚያስችሉ የተለያዩ ምልክቶችን ማወቅና ለማርገዝ የሚደረገውን ሙከራ በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ማድረግ የማርገዝን እድል ይጨምራል።፡ይህንን ጊዜ መገመት ከሚያስችሉት ዘዴዎች አንዱና ቀለል ያለው ቀን መቁጠር ነው፡፡ እንደ የወር አበባ ኡደት ሁሉ የኦቩሌሽን ጊዜም ከሴት ሴት እንዲሁም አንድ ሴት ላይ ከወር ወር የተለያየ ስለሆነ ይህ ነው ብሎ አንድን ቀን መጠቆም አይቻልም። በአማካይ የወር አበባቸዉ ኡደት ከ28-32 ቀን  ለሆነ ሴቶች ኦቩሌት ያደርጋሉ ተብሎ የሚገመተው ያለፈው የወር አበባቸው ከጀመረበት  ቀን በኋላ ከ11ኛው እስከ 21ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ጊዜ ለእርግዝና ምቹ ጊዜ ተብሎ ይታወቃል።

ከላይ እንደተገለጸው ከኦቩሌሽን በኋላ እንቁላሉ ለፈርቲላይዜሽ (ለእርግዝና) ብቁ ሆኖ የሚቆየው ከ12-24 ሰአት ያህል ቢሆንም የወንድ ዘር ግን ከግብረስጋ ግንኙነት በኋላ በሴቷ ሰውነት ውስጥ ከሶስት እስከ አምስት ቀን መቆየት ስለሚችል እርግዝና ሊፈጠር የሚችልባቸውን ቀናት ሰፋ ያደርገዋል፡፡ ለእርግዝና ምቹ ነዉ ተብሎ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ዉስጥ በየቀኑ አሊያም አንድ ቀን እየዘለሉ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ የማርገዝን እድል ያሰፋል፡፡ ከግንኙነት በኋላ በጀርባ ተኝቶ ከ10-15 ደቂቃ መቆየት የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን በር ለመግባት በቂ ጊዜ ይሰጠዋል። በተቃራኒዉ ማርገዝ ለማይፈልጉ ደግሞ ኦቩሌሽን ከሚጠበቅበት 3-5 ቀናት በፊት ጀምሮ እንዲሁም በኦቩሌሽን ወቅትም ግንኙነት አለማድረግ ይመረጣል። ኮንዶም ወይም ሌሎች የእርግዝና መከላከያ መንገዶችም ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡ ጤናማ የወንድ ዘር የእርግዝናን እድል ለመጨመር ስለሚረዳ ለማርገዝ ሙከራ በሚደረግበት ጊዜ ወንዱ አልኮል መጠጥን በመቀነስ፤ ሲጃራ በማቆምና የሰውነት ክብደትን በመቆጣጠር የበኩሉን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ሌላስ ጊዜ ቢሆን ባይጠጣና ባይጨስ አይሻልም?

ሌሎች ኦቩሌሽንን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶች ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት መካከል የማህጸን ፈሳሽ መጠን መጨመር፤ ባንዳንድ ሴቶች ላይ በኦቩሌሽን ወቅት በአንደኛው ጎናቸው ህመም ቢጤ መሰማት እና በሌሎች ላይ ከሚቀጥለው የወር አበባ በፊት መሀከለኛው ቀን አካባቢ ትንሽ ደም መፍሰስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በሃገራችን መኖሩን እንጃ እንጂ ለቤት ውስጥ መጠቀሚያ የሚሆን ኦቩሌት መደረግ አለመደረጉን የሚጠቁም መመርመሪያ መሳሪያም አለ፡፡ ቀን መቁጠር ከደከማችሁ ፋርማሲ ሄዳችሁ መኖር አለመኖሩን መጠየቅ ወይም ዳያስፖራ ዘመዳችሁን አደራ አምጣልኝ ማለትም ይቻላል!

እርግዝና መከሰት/መጀመር አለመጀመሩን ለማወቅ የሚቀጥለው የወር አበባ መምጫ ጊዜ እስኪደርስ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ በተጠበቀበት ጊዜ ካልመጣ የእርግዝና ምርመራ ማድርግ፤ ከመጣ ደግሞ በሚቀጥለው ዙር ተመሳሳይ ሙከራ መቀጠል፡፡

የኦቩሌሽን ጊዜ በትክክል ባለመታወቁ የተነሳ ሙከራ በተደረገ በመጀመሪያው ወር ላይረገዝ ይችላል፡፡ ስለዚህም ደጋግሞ መሞከር ይመከራል፡፡ እድሜያቸው ከ35 አመት በታች ለሆኑ ከአንድ አመት ሙከራ በኋላ፤ ከዛ በላይ ለሆኑ ደግሞ ከስድስት ወር ሙከራ በኋላ እርግዝና ካልተፈጠረ በዘርፉ የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎችን ማማከር ይበረታታል፡፡

እርግዝና ሲታቀድ ቢያንስ ከወር በፊት ፎሊክ አሲድ የተባለውን ንጥረ ነገር ከመድሃኒት ቤት ገዝቶ መጠቀም መጀመር ጤናማ ልጅ ለመውለድ የላቀ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

ይቅናችሁ እንግዲህ! ለገንፎ መጥራት እንዳትረሱ ታዲያ!
በመጨረሻም - መቼም አንድ ቀን ስለልጅ መዉለድ ማሰባቸዉ አይቀርምና ሼር በማድረግ ለወዳጅ፣ ዘመድና ጓደኛ እንድታካፍሉ በማክበር እንጠይቃለን! ጥያቄዎቻችሁንና አስተያየታችሁን በኮሜንትም ሆነ በፌስቡክ ፔጃችን ብትልኩልን እናስተናግዳለን።
5 سال پیش در تاریخ 1398/06/18 منتشر شده است.
85,732 بـار بازدید شده
... بیشتر