ሎዶቅያ ክፍል 1 | ሰባቱ አብያተክርስቲያናት | ፓስተር አስፋው በቀለ www.operationezra.com

Asfaw Bekele Official
Asfaw Bekele Official
11.5 هزار بار بازدید - 4 سال پیش - በሎዶቅያ፡ ለመንፈሳዊ ነገሮች ግድ ያልነበራት
በሎዶቅያ፡ ለመንፈሳዊ ነገሮች ግድ ያልነበራት (ለብ ያለች) ሀብታም ቤተ ክርስቲያን (ራእይ 3፡14-22)። የሎዶቅያ ከተማ በሀብቷ የታወቀች ነበረች። ባንኮች የተስፋፉባት፥ ልዩ ጥቁር የሱፍ ልብሶች የሚመረቱባት፥ እንዲሁም የታወቀ የሕክምና ትምህርት ቤት የሚገኝባት ከተማ ነበረች። ይህ የሕክምና ትምህርት ቤት በተለይ በዓይን ሕክምና ምርጥ መሆኑ ይነገራል። ችግሩ በከተማይቱ ውስጥ ጥሩ የውኃ አቅርቦት አልነበረም። ወደዚህች ከተማ ውኃ የሚመጣው ከስምንት ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዞ ነበር። ውኃው ወደ ከተማይቱ በሚገባበት ጊዜ ለብ ስለሚል፥ ለመጠጥ አይመችም ነበር። የሎዶቅያ ነዋሪዎች ለነገሮች ብዙም ስሜት ያልነበራቸውና ሁልጊዜም የሌሎችን ፍላጎቶች ፍላጎታቸው ለማድረግ የሚጥሩ ነበሩ። በሀብታቸው ምክንያት የራስ ብቃት የነበራቸው ስለሆነም፥ ብዙውን ጊዜ ከተማይቱ በመሬት መንቀጥቀጥ በምትደመሰስበት ጊዜ የሌሎችን እርዳታ ሳይሹ ራሳቸው ይገነቧት ነበር። የሚያሳዝነው ይኸው የትዕቢት፥ በራስ የመመካትና የግዴለሽነት አመለካከት በቤተ ክርስቲያኗም ውስጥ ይታይ ነበር። አማኞቹ ክርስቶስን በሙሉ ልባቸው አይከተሉትም ነበር። እነዚህ አማኞች በቂ ገንዘብ ያላቸው በመሆናቸው የተሳካልን ነን ብለው ያስቡ ነበር። እግዚአብሔር በእኛ ደስ ባይሰኝ ኖሮ እንዴት ሀብታም ልንሆን እንችል ነበር? ብለው ያስቡ ነበር። ነገር ግን አማኛቹ በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት ምን እንደሚመስሉ አልተገነዘቡም ነበር። እግዚአብሔር ሲያያቸው ድሆች፥ የተራቆቱና ለመንፈሳዊ ዓይናቸው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ነበሩ። እግዚአብሔር እንዲረዳቸው፥ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያበለጽጋቸው፥ ጽድቁን እንዲያለብሳቸውና መንፈሳዊ እውነቶችን የሚመለከቱበትን ዓይን እንዲሰጣቸው ከፈለጉ፥ መለወጥ ያስፈልጋቸው ነበር። ራሳቸውን አዋርደውና የነበሩባቸውን ችግሮች ተረድተው እግዚአብሔር ጽድቅን፥ መንፈሳዊ ዓይኖችንና መንፈሳዊ ጤንነትን እንዲሰጣቸው መጠየቅ ያስፈልጋቸው ነበር። ክርስቶስ በልባቸው እና በቤተ ክርስቲያናቸው ደጅ ላይ ቆሞ ነበር። ወደ ውስጥ ገብቶ ከእነርሱ ጋር ኅብረት ለማድረግ ይፈልጋል። ነገር ግን ችግራቸውን ተረድተው በራቸውን መክፈትና እርሱን ወደ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋቸው ነበር። ይህን ካላደረጉ፥ ክርስቶስ በፍርድ ከአፉ እንደሚተፋቸው ያስጠነቅቃቸዋል። ይህም በከተማቸው ውስጥ የሚገኘውን ውኃ ከቀመሱ በኋላ ከሚተፉበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ነበር። ንስሐ ገብተው ከክርስቶስ ጋር የነበራቸውን ግንኙነትና ኅብረት፥ ካደሱ፥ ክርስቶስ በዘላለማዊ መንግሥቱ ውስጥ የመግዛትን መብት እንደሚሰጣቸው ቃል ይገባላቸዋል።
4 سال پیش در تاریخ 1399/04/18 منتشر شده است.
11,553 بـار بازدید شده
... بیشتر