Yosef Kasa Ethiopian Amharic Protestant Mezmur(መኖር አልችልም)

Christian lyrics
Christian lyrics
23.8 هزار بار بازدید - 4 سال پیش - ሁልጊዜ ፡ ምናፍቅህየነፍሴ ፡ ጥማት
ሁልጊዜ ፡ ምናፍቅህ
የነፍሴ ፡ ጥማት ፡ የምትወድህ
ልዑል ፡ ነህ ፡ ለእኔ
እርሱ ፡ ነው ፡ ረሃቤ

ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም
ታውቃለህ ፡ አቅም ፡ እኔ ፡ የለኝም
ኢየሱሴ ፡ የእኔ
አትሂድብኝ ፡ ከእኔ

አዝ፦ አትሂድብኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝም (፪x)

ባጠፋም ፡ ልጅህ ፡ ነኝ ፡ ቅጣኝ
ግን ፡ መንፈስህ ፡ እንዳይርቀኝ
የሕይወት ፡ እስትንፋሴ
ህልውናህ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ

ስትርቀኝ ፡ ይከፋኛል
አንተን ፡ መፍራት ፡ ይከብደኛል
የምትረዳኝ ፡ ረድኤቴ
አትሂድ ፡ ከሕይወቴ

አዝ፦ አትሂድብኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝም

ዝናህ ፡ ሀብት ፡ ሞልቶ ፡ ጐተራዬም ፡ ቢሞላም ፡ አዬ
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ(፪x)

መኖር ፡ ይከብደኛል ፡ ሕይወትም ፡ ይታክተኛል
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጎኔ(፪x)

አባብዬ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ ጠዋትም ፡ ማታ
ህልውናህ ፡ መገኘት ፡ ደስታን ፡ አጠገበኝ ፡ ፊትህ (፪x)

ፊትህን ፡ ሳየው ፡ ውስጤን ፡ ደስታ ፡ ትሞላኛለህ
ምንም ፡ ባይኖረኝ ፡ ምንም ፡ አንተው ፡ ትበቃኛለህ (፪x)

መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ
መኖር ፡ አልችልም ፡ እኔ ፡ ስትለየኝ ፡ ከጐኔ (፭x)
4 سال پیش در تاریخ 1399/05/16 منتشر شده است.
23,826 بـار بازدید شده
... بیشتر