የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በልሳን መናገር ግንኙነት አላቸውን?

Zelalem Mengistu
Zelalem Mengistu
8.7 هزار بار بازدید - 5 سال پیش - የዚህ፥ 'የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በልሳን
የዚህ፥ 'የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በልሳን መናገር ግንኙነት አላቸውን?' የሚለው ትምህርት ዋና አሳብ ይህ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተግባር አማኝን ከአካሉ፥ ከክርስቶስ አካል፥ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ማቆራኘት ነው።

መቼ ነው አንድ ሰው የክርስቶስ አካል ክፍል የሚሆነው? ሲያምን። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በሙሉ በመንፈስ ተጠምቀው ነበር? በእርግጥ ተጠምቀዋል። ሁሉስ በልሳኖች ይናገሩ ነበር? አይናገሩም። ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅና በልሳኖች መናገር ይቆራኛሉ? የለም፤ አይቆራኙም።  

ልክ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ልሳኖች ቁርኝት እንደሌላቸው ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳኖችም ቁርኝት የላቸውም። የመንፈስ ጥምቀት አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን፥ ዳግም ሲወለድ ወደ ክርስቶስ አካል የሚገባበት ሥርዓት ነው።

የቃሉን ትምህርት በሰውኛ ልምምድ እየሸቃቀጥን ቃሉን ትተን ልምምዶችን ማስተማርና ማለማመድ የለብንም። ቃሉን እንማር፤ ቃሉን እናስተምር፤ ቃሉን እንታዘዝ። ይህንን እንድናደርግ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ይርዳን።
5 سال پیش در تاریخ 1397/11/26 منتشر شده است.
8,787 بـار بازدید شده
... بیشتر