አካል ጉዳተኛ ነኝ ብዬ መለመን አልፈልግም!

EMAT GURAGE MEDIA
EMAT GURAGE MEDIA
4.4 هزار بار بازدید - 3 سال پیش - "አካል ጉዳተኛ ነኝ ብዬ መለመን
"አካል ጉዳተኛ ነኝ ብዬ መለመን አልፈልግም" ከአዲስ አበባ 220 ኪ.ሜ ርቄ አቦጋዴ በተሠኘች ቀበሌ ውስጥ ከ ወጣቷ በሰዓቷ ጋር ተገናኝቻለሁ። በሰዓቷ ገና የወራት ህፃን እያለች በሶስት አመት የሚበልጣት ታላቅ ወንድሟ አዝሏት እየተጫወተ ቆይቶ ... በኋላም ሜዳ ላይ እንዳስቀመጣት ዝናብ ሲመጣ ረስቶ ወደ ቤት እንደገባና እሷም ዝናቡ ና ጎርፉ በላይዋ ላይ እንደወረደ ነግራኛለች። ከዚህ በኋላም ጤናዋ ተቃወሰ ና አካል ጉዳተኛም ሆነች። ወላጅ አባቷ ከሞቱ የቆዩ ሲሆን ከታላቅ ወንድሟና ከእናቷ ጋር ትኖራለች። ወንድሟም የራሱን ጉሮሮ ከመሸፈን የማያልፍ በመሆኑ የእናቷም አቅመ ደካማነት ተጨምሮበት ወጣቷና አካል ጉዳተኛዋ በሰዓቷ ቤተሰቦቿ ሊደግፏት ሲገባ እሷ ግን ደጋፊያቸው ነች። ቤተሰቦቿን ለመርዳት አካል ጉዳተኛ ነኝ ብላ ልመና ማውጣት መቼም እንደማታስብ ስትነግረኝ ተደምሜያለሁ። እሷ መስራት ነው የምትፈልገው። ከገብያ እናቷን እየላከች ክብሪት ፣ ጨው ፣ ስኳር .. የመሣሠሉ ነገሮችን የመቶም ይሁን የሁለት መቶ ብር ታስመጣና በሯ ላይ ተቀምጣ ይሄንኑ ለሠፈሯ ሠዎች ትቸረችራለች። እንዲህ እየነገደች ቢያንስ ጠግቦ መብላት ህልሟ ቢሆንም አቅም ስለሌላት የሰፈሩ ሰው ከሚጠይቃት ነገሮች ለ አብዛኞቹ መልሷ "የለኝም" አልያም "ብር አጥቼ አላመጣሁም " ነው:: እኔም ለማበረታታት ያህል ምን ልግዛሽ ስላት "ዛሬ ምንም የለኝም " ነበረ መልሷ። የአእምሮዋ ብስለት ከአለመማሯ ና እዚሁ በር ላይ ቁጭ ብላ እንደመዋሏ የሚታመን አይደለም። ሁላችንም የአቅማችንን ብናግዛት በእርግጠኛነት ትልቅ ነጋዴ ሆና እንኳን ለራሧ ለሰውም ትተርፋለች። ለ እህቴ የምትችሉትን እንድትደግፏት እማፀናለሁኝ። ስልኳ 0978148170 አካውንት ፈትወድ ባዶረ (እናቷ) ንግድ ባንክ 1000423845825
3 سال پیش در تاریخ 1400/06/03 منتشر شده است.
4,481 بـار بازدید شده
... بیشتر