የአሁን ሃይል The Power of Now Book Summary In Amharic | Book Review in Amharic Ethiopia

Henok Hirboro
Henok Hirboro
28.9 هزار بار بازدید - 2 سال پیش - The power of now(የአሁን ሃይል)
The power of now(የአሁን ሃይል) መጽሃፍ፣ መንፈሳዊና ስነ ልቦናን አጣምሮ የያዘ መጽሃፍ ሲሆን፣ ሰዎች ከራሳቸውና ከሌሎች ጋር እንዴት ጤናማ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል በስፋት ያቀርባል።

የመጽሃፉ ጭብጥ፣ አሁን ያለው ጊዜ ብቻ ነው እውነተኛና ጠቃሚ(only the present moment is real and matter.) ይላል። ያለፈውና የወደፊቱ በሃሳባችን የተፈጠሩ ናቸው። ሰዎች ህይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ(control) መጠየቃቸው የሚያመጣው ትርፍ ቢኖር ህመምና ቅዥት ብቻ እንደሆነ ይገልጻል።

እንዲሁም በ አሁን ጊዜ (in the present moment)ራሳቸውን እንዲይዙ(እንዲሆኑ) ለመርዳት የመዝናናትና የማሰላሰል(meditation) ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ይጠቁማል።

ሙሉ መጽሃፉን  ለማንበብ 👉 https://t.me/henokhirboro

▼ FOLLOW ME  ▼

     • Instagram : https://www.instagram.com/
     • Facebook : Facebook: henokhirboro
     • Telegram : https://t.me/henokhirboro
     • TikTok : https://www.tiktok.com/henokhirboro
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------
መግቢያ፥-

የዛሬ የመጽሃፍ ቅምሻችን እ አ አ በ1999 ለሁለተኛ ጊዜ በታተመ ወቅት የጋዜጠኞች ቁንጮና ንግስት በሆነቹ opera wenfrey ሊነበቡ ከሚገባቸው የክፍለ ዘመኑ ድንቅ መጽሃፍ ስትል ከመረጠችው በኋላ በሰሜን አሜሪካ ብቻ እስከ 2009 ባለ ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን copy በላይ ለመቸብቸብ በቅቷል።

በ New York times(በመጽሃፍት ሽያጭ) bestselling books  በመባል አንደኝነት ደረጃን መቆጣጠር የቻለና፣ ከ 33 በላይ በሚሆኑ የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ፣ ተወዳጅነትን ያተረፈውን የ ኢካርት ቶሌ  the power of now (የ አሁን ሃይል) የሚለው መጽሃፍ ነው።

ስለ ደራሲው(ኢካርት ቶሌ)፥-

በመግቢያ ላይ የሰማችሁት አሳዛኝ ታሪክ የዚህ መጽሃፍ ደራሲ የ ኢካርት ቶሌ ነበር። ቶሌ ትውልዱ ጀርመናዊ ሲሆን የመንፈሳዊ፣ ሜታፊዚክስ፣ እንዲሁም የself-help መጽሃፍት ደራሲ ነው።
እ አ አ 1977 በ 29 አመቱ በ አንድ ምሽት ከገጠመው እሱ) መንፈሳዊ ልምምድ) ከሚለው መገለጥ የተነሳ ፣ ውስጣዊ ለውጥ በማግኘቱና ከነበረበት ከባድ የጭንቀት በሽታ ከዳነ በኋላ ስሙን ከ ኤልሪክ ወደ ኤክህርት በመለወጥ በ አለም ዙሪያ ተወዳጅ የሆነውን የመጀመሪያ መጽሃፉን the power of now(የአሁን ሃይል) 1997 በቅቷል።

The power of now(የ አሁን ሃይል) መጽሃፍ መንፈሳዊና ስነ ልቦናን አጣምሮ የያዘ መጽሃፍ ሲሆን፣ ሰዎች ከራሳቸውና ከሌሎች ጋር እንዴት ጤናማ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል በስፋት ያቀርባል።
ራስን የማሰላሰል(self-reflection)ና በ አሁን ጊዜ የመገኘት ጽንሰ-ሃሳብ(present in the moment) መርሆችን ቀለልባሉ ምሳሌዎች ያሳያል።

የመጽሃፉ ጭብጥ፥-

አሁን ያለው ጊዜ ብቻ ነው እውነተኛና ጠቃሚ(only the present moment is real and matter.) ይላል። ያለፈውና የወደፊቱ በሃሳባችን የተፈጠሩ ናቸው። ሰዎች ህይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ(control) መጠየቃቸው የሚያመጣው ትርፍ ቢኖር ህመምና ቅዥት እንደሆነ ይገልጻል።

እንዲሁም በ አሁን ጊዜ (in the present moment)ራሳቸውን እንዲይዙ(እንዲሆኑ) ለመርዳት የመዝናናትና የማሰላሰል(meditation) ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ይጠቁማል።
ከእነዚህም መካከል ብዙ ተግባራትን በማስቀረት፣ ፍጥነት መቀነስ፣ ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ እንዲሁም ስለ ወደፊቱ ያለ ጭንቀቶችን መተው ያካትታል።

የመጽሃፍ ሁለት ቁልፍ - ጽንሰ ሃሳቦች

የመጀመሪያው 1  እኛ አእምሮ አችን አለመሆናችን ነው። (we are not our mind)
አብዛኞቻችን አውቀን(consciously) አእምሮአችንን አንጠቀምም።
ይልቁንም አእምሮአችን በማያቋርጥ ሃሳቦች እኛን ይቆጣጠረናል። ብዙ ጊዜም በእኔነት(ego-self) እንመራለን። Egoአችን ስለራሳችን ያለን አመለካከት ካለፈው ልምምዳችን እየቀዳ ፣ መሆን ስለምንፈልገው ደግሞ ከመጪው ጊዜ ይመገባል።   ስለ ራስህ ያለህ አመለካከት ያለፈው ህይወት ድምር ውጤት ከሆነና መጪውን ጊዜም ከዚህ መነሻ የምታይ ከሆነ  በጊዜ ቅዥት ውስጥ ገብተሃት። አላፊውም ሆነ መጪው ያለው አእምሮው ውስጥ ነው።

አብዛኛው ጉልበታችንን የምናሳልፈው ባለፈው አሊያም በመጪው ጊዜ ላይ እንጂ በአሁኑ ጊዜ አይደለም።
ብዙ ጊዜ እምቅ አቅማችንና ሃይላችን የሚያልቀው ከ አሁን (present moment)  
ይልቅ በ አለፈው(ልንለውጠው በማንችለው) ወይም በመጪው(በማናውቀውና እርግጠኛ መሆን በማንችልበት) ላይ መሆኑ ያሳዝናል።

ብዙዎቻችን አሁን ላይ የለንም(Absent) ነን። በአእምሮአችን ሃሳብ አለም ያለፈው ጊዜ ላይ አለኢያም ደግሞ ስለመጪው በማሰብና በመጨነቅ እንቆያለን። በዚህም ሁልጊዜ የ አሁንን ሃይል በማባከን ተጠምደናል።

የ አሁን እርግጠኛ ልትሆንበትና እውነት(real) የሆነ ጊዜ ነው።    ህይወት ሁሌ የምታስጨንቀንና የምታስፈራራን በማናውቀውና እውን ባልሆነ በመጪውና በወደፊት ጊዜ ላይ ቆማ ነው። በትላንትናና በዛሬ ላይ ምንም ስልጣን እንደ ሌላት ታውቃለች። ማንም ሰው ስለመጪው እንጂ ስላለፈው ሊጸጸት ይችል ይሆናል እንጂ ሊጨነቅ አይቻልም። ዛሬም ቢሆን በእጅ ያለች ቀን ናት አሁን ደግሞ ከዛሬ ይልቅ ሃይል አላት።

ሁለተኛው 2 እራሳችንን ከ አእምሮአችን እንዴት ነጻ እናደርጋለን(how do we free ourselves from our minds?) አእምሮህን(የምታስበውን ሃሳብ) በንቃት ተከታተል(observe your mind)
ይህ ማለት (የምታስበውን አስብ) እንደሚሉት ማለት ነው።  ካለፈው ጊዜ ትኩረትህን ሰብሰብ  በመጪው ጊዜ በሃሳብ ከመንጓዝ ለሃሳብህ ሉጋም አበጅለት።  ከማያስፈልጉ የትላንት ትዝታዎች ከማታውቀው ከመጪው ጊዜ ፍርሃት አእምሮህ በአሁን ላይ ይሁን። ትኩረትህን በ አሁን ላይ መሰብሰብን ተማር።
አእምሮህ በትላንት እንዲያላዝን ፣ በመጪው ደግሞ በፍርሃት እንዳይቆዝም ሁሌ አሁን ላይ አድርገው።

ስሜትህን ተመልከት(watch your emotion)የሰው ልጅ በቀን ከ 60.000 በላይ ሃሳቦች እንደ ሚያስብ ጥያቶች ያሳያሉ። እነዚህን ሁሉ ሃሳቦች መቆጣጠርና በንቃት መከታተል እጅግ በጣም ከባድና አድካሚ ነው።   ሁሉንም ሃሳቦች መከታተል ስለማንችል፣ ሀሳቦች በስሜት(emotion)በኩል እራሳቸውን ስለሚገልጡ፣  ስሜታችንን(emotion)ናችንን በንቃት መከታተል እንችላለን። ይህም አእምሮ አችን አሁን ላይ እንዲሆን ለማስገዛት ይረዳናል።

   ለ አሁን ተገዛ (surrender to the present) አንዳንድ ያለፉ የህይወት ልምምዶቻችን ህመምን እና አሉታዊ ውጤትን ይፈጥሩብናል። በዚህም አሉታዊ  ሃይል ይጨምራል።  ለ አሁን መገዛት እጅ መስጠትን፣ ድክመትን ወይም ሁሉን መተው ማለት አይደለም። ይልቁኑ ጤናማ ያልሆኑና አሉታዊ የትላንት መርዛማ ትዝታዎች ያለፈው ጊዜ ላይ ባሉበት መጣል እና ከ አሁን ሃይል ጋር መገናኘት ነው።

-----------------------------------------------------

የመጽሃፉ ደራሲ አሳዛኝ ታሪክ - 00:00
መግቢያ - 02:31
የመጽሃፉ ጭብጥ - 04:14
እኛ አእምሮአችን አይደለንም - 05:12
ከአእምሮ ነጻ መውጣት - 07:14
የምታስበውን አስብ - 07:29
ስሜትህን ተመልከት - 08:09
ለአሁን ተገዛ - 08:50
ማጠቃለያ - 09:24
ስንብት - 10:19
2 سال پیش در تاریخ 1401/04/25 منتشر شده است.
28,928 بـار بازدید شده
... بیشتر