የኔ ብቸኛ ሳሚ-ዳን; YENE BICHEGNA, SAMI-DAN; NEW ETHIOPIAN MUSIC VIDEO

Sami Dan
Sami Dan
33.7 هزار بار بازدید - 2 سال پیش - የኔ ብቸኛየትም ዞሬ ስደርስ ደጃፍ
የኔ ብቸኛ

የትም ዞሬ ስደርስ ደጃፍ ግርጌ
እጣራለሁ ስምሽን ከፍ አድርጌ
ካለሽ መልካም ከሌለሽ ነው ጉዱ
በድን ቤትን ይከብዳል መልመዱ

አንቺ ሁሌ እኔኑ ጠባቂ
ቀን ይበራል አይተሽኝ ስትስቂ
ያኔ ሁሉም ለኔ ይስተካከላል
መኖርሽ ብቻ ያኖረኛል

ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ
አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ
ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ (4x)

በእውቀት ቀለም ብሆን የመጠኩኝ
በስልጣኔ ሀገር ያስጨነኩኝ
ይሄ ሁሉ አንቺን መች ሊገርምሽ
ሁሌም ልጅ ነኝ እኔ ላንቺ ልጅሽ

በመንገዴ ፀሎትሽ ይቀድማል
ስንቱን ችግር ይዞ ያሻግረኛል
ምንም ብሆን ነብስያሽ ይነግረኛል
ስለኔ ብለሽ ስንቱ ውስጥ ገብተሻል

ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ
አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ
ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ (4x)

ነብስን በሚገርፈው በሀሩር በብርዱ
ጠብ የሚል ባይገኝ ባይቀናም መንገዱ
አንቺ ግን ስለኔ ሁሉንም ቧጠሻል
ፍቅርሽ ወሰን የለው ምንስ ያግድሻል

ልጄ ልጄ እያልሽ ስላንቺ ሳትኖሪ
ቤቱ እንዳይጓደል ቀልጠሽ የምትበሪ
ውለታሽ ቢበዛ አንድ ሆነ ፀሎቴ
አንቺን ያቆይልኝ ያኑርሽ እናቴ እማማ

ኡ እናትዬ ማማዬ…..
ኡ እናትዬ……………..

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ (4x)
2 سال پیش در تاریخ 1401/02/17 منتشر شده است.
33,761 بـار بازدید شده
... بیشتر