የጅማው መንዝ ሙዚቃ ቤት ትዝታ

Ethiowork - ኢትዮወርቅ
Ethiowork - ኢትዮወርቅ
1.3 هزار بار بازدید - 2 سال پیش - በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀደምቱ የሙዚቃ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀደምቱ የሙዚቃ ካሴት አሳታሚ
የጅማው መንዝ ሙዚቃ ቤት
(በወርቅአፈራው ያለው _ ጅማ ፋና ኤፍ ኤም 98.1)

ከከሁለት እና ከሦስት አስርት አመታት በፊት በጅማ ከተማ ስለነበሩ ሙዚቃ ቤቶች ስናወሳ መንዝ መዚቃ ቤትን አንዘነጋም።

መንዝ ሙዚቃ ቤት  በአስቴር አወቀ ሀገሬ የተሰኘውን ኦሪጅናል  ካሴት በ1975 ዓ. ም በማከፋፈል ስራውን እንደ ጀመረ የሙዚቃ ቤቱ ባለቤት የነበሩት ዛሬ በህይወት የሌሉት የአቶ በቀለ  ለማ  ልጅ ምናለሻው በቀለ ነግራኛለች።
ሙዚቃ ቤቱ በወቅቱ ፣ በየጊዜው የሚወጡ ካሴቶችን ለህበረተሰቡ በሽያጭ ከማቅረብ(ከማከፋፈል) ባሻገር በተለያዩ ጊዚያት ባሳተማቸው የሙዚቃ ካሴቶች የሚታወስ ነው።

ካሴት በማሳተም በጅማ ከተማ እና አከበቢው ብቻ ሳይሆን  በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም ብቸኛ እና ቀዳሚ የነበረ ሙዚቃ አሳታሚ  እንደነበረ ይነገራል።
የሙዚቃ ካሴት ህትመት ጉዞ

የመንዝ የሙዚቃ ካሴት ህትመት ጉዞ የጀመረው በ19 78 ዓ.ም የፖሊስ ሆኬስትራ ዘፋኝ የነበረችውን የአልማዝ ተፈራን "ጅማ ላይ ነው ቤቱ " የተሰኘውን የሙዚቃ ካሴት በማሳተም ሲሆን፣በመቀጠል የእያዩ ማንያዘዋልን 'አይናማ" 1980 ዓ.ም፣ የአልማዝ ተፈራን ቁጥር ሁለት ካሴት በ1980 ዓ.ም ፣ የክፍሌ በቀለን "ተመከሪ"  በ1984 ዓ.ም እና 1987 ዓ.ም የሻፊ መሐመድ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ካሴት አሳተመ።
ባጠቃላይ 5 ካሴቶችን ለሳትም በቅቷል።
የጅማ ሙዚቃ ቤቶች ሲነሱ መንዝ አስታውሶ የሙዚቃ ቤቱ ባለቤት የነበሩትን ሰው ፣ያአቶ በቀለ ለማን አስተዋፆ እና ለሞያው ያላቸውን መሰጠት አለማውሳት ንፉግነት ነው።ልጃቸው ምናለሻው በቀለም ይህን እውነት ተናግራ አትጠግብም። የሚያውቋቸው የከተማው ነዋሪዎች ምስክር ነን ብለውኛል።

ለዛም ይመስላል የቀድሞው መንዝ ሙዚቃ ቤት አሁን ወደ መንዝ መድኃኒት ቤት ቢቀየርም ፣ የያኔው ዘመን የሙዚቃ የሚይያስታውሱ አሻራዎች በልጆቻችው መቀጠላቸው።
አቶ በቀለ ለማ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 26 አመታት ቢያስቆጥሩም ፣አሻራዎቻችው እንዳይጠፉ ፣ የሚዚቃ ቤቱን ማስተር ኬሴቶች፣ማጫውቻ ቴፖች፣እና የመሳሰሉትን የሙዚቃ ቤቱን ቁሶች በክብር ስለማኖሯ ልጃቸው ምናለሸዋ በቀለ ነግራኛለች።

እሷ እንደምትለው እነኚ ቁሶቹ ዛሬ በዲጂታል ዘመን እንኳን ብርቅ ናቸው።ከአመታት በኃላ ታሪክ ነጋሪ መሆናቸው ስለማይቀር እንደ የጅማ ህዝብ ቅርስ  ነው የምቆጥራቸው ብላለች።ለወደፊት አይታወቅም ካሴት እና ቴፕ የሚፈልጉብት ወቅት ይመጣል።ስለዚህ ለትውልድ ለማሻገር በእንክብካቤ አኑሪያቸዋለሁ ብላለች ምናለሸዋ በቀለ።
እናም ...ቀደምቱ መንዝ ሙዚቃ ቤት አሁንም በብዙዎች ዘንድ ይታወሳል።
2 سال پیش در تاریخ 1401/01/20 منتشر شده است.
1,390 بـار بازدید شده
... بیشتر