Alemayehu Eshete - ስቀሽ አታስቂኝ - Sikesh Ataskigne

Cannybird
Cannybird
569.8 هزار بار بازدید - 10 سال پیش - Listen, upload and share your
Listen, upload and share your favorite tracks at https://www.ethiomusica.com
------------------------------------------------
ግጥም እና ዜማ - ኮሎኔል ግርማ ሃይሌ ( ፒያኖ ተጫዋች )
Lyrics and Melody - Colonel Girma Haile ( Pianist )  

አለማየሁ እሸቴ እንደተናገረው ይህ ሙዚቃ መጀመሪያ በሙሉ ባንድ የተሰራ ሲሆን ብዙም አትኩሮት አልሳበም ነበር፤ በኋላም የሁዳዴ ጾም ዋዜማ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስቱዲዮ ውስጥ በኪቦርድ ታጅቦ የተጫወተው ይህ ሙዚቃ እጅግ ተወዳጅና ተደማጭ ሊሆን ችሏል። ሙዚቃውን ሲጫዎትም እናት ኢዮጵያን እያሰበ ነበር። የሙዚቃው ደራሲ ኮሎኔል ግርማ ሃይሌ ከአራት ወይም ከአምስት አመት በፊት ከዚህ አለም በሞት መለየቱንም ገልጿል።
--------------------------------------------------------------------------
እኔ ልኮራመት እኔ ከሰል ልምሰል
ስቀሽ አታስቂኝ የደላሽ ይመስል
ሁሉን አውቀዋለሁ የእምዬ'ኮ ልጅ ነሽ
ሞተሽ ታርፊዋለሽ አንድም ቀን ሳይደላሽ
እኔ ልኮራመት እኔ ከሰል ልምሰል
ስቀሽ አታስቂኝ የደላሽ ይመስል
ሁሉን አውቀዋለሁ ግማሽ አካሌ ነሽ
ሞተሽ ታርፊዋለሽ አንድም ቀን ሳይደላሽ
እሽሩሩ የሚልሽ አባትሽ መንኩሶ
ምስጥ ያሳድግ ጀመር ድንጋይ ተንተርሶ
ጥፋተኛ እናትሽ ወልዳሽ የሞተችው
ላንቺ ጡት ሰስታ ለትል አጠጣችው
ትፍጨረጨሪያለሽ ወጉ አይቅር ብለሽ
አልቃሽ አጣሽ'ንጂ ቆይተሻል ከሞትሽ
እህት አበባ ክንዴ የምልሽ ወንድምሽ
ካንቺ ያልተሻልኩኝ ነኝ ምናባቴ ላርግሽ
የጎረቤት ምግብ እያሸተትሽ ኑሪ
ለመብላት መብት የለሽ መቼም አትጠሪ
ውለታ እስካልመለስሽ ማነው የሚያበላሽ
የእምዬ ልጅ ቁረጭ ችጋር ያንፈራፍርሽ።
10 سال پیش در تاریخ 1393/10/21 منتشر شده است.
569,835 بـار بازدید شده
... بیشتر